ዉድ የፒራሚድ አካዳሚ ወላጅ ፣ ተማሪዎች እንዲሁም የት/ቤቱ ሠራተኞች ት/ቤቱ አሰራሩን አዘምኖ ዘመኑ ወደ ደረሰበት ቴክኖሎጂ ( Digital School Management System ) አሰራሩን ለመቀየር እንዲሁም በወላጅ ፣ ተማሪዎች ፣ መምህራን እነ የት/ቤቱ አስተዳደር ክፍል ጋር ያለውን ግንኙነት ቀላል እና ዘመናዊ ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል ። አገልግሎቱን ለማስጀመር የተማሪዎች እንዲሁም የት/ቤቱ ሠራተኞች መረጃ መሰብሰብ ግድ ስለሆነ ሁላችሁም ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገፅ በመግባት [ Sign Up ] የሚለውን ቁልፍ በመጫን በመቀጠል የምትገኙበትን ቅርንጫፍ ት/ቤት በመምረጥ ቀጥሎ የሚመጠጣውን የመረጃ መጠይቅ ሁሉንም በጥንቃቄ በመሙላት [ Submit ] የሚለውን ቁልፍ በመጫን መረጃውን ያስተላልፉ ። አገልግሎቱ ከሰኞ 19/02/2016 ጀምሮ አ-አ በዋናው ግቢ በሚገኙ የ8ተኛ ክፍል ተማሪዎች የሙከራ መርሃ ግብር ስለሚጀመር በዋናው ግቢ የምትገኙ የ8ተኛ ክፍል ተማሪዎችና መምህራን በአስቸኩዋይ መረጃችሁን እንድታስተላልፉ እናሳስባለን ። በሌሎች ቅርንጫፍ ት/ቤት የምትገኙ ተማሪዎች እንዲሁም የት/ቤቱ ሠራተኞችም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ መረጃችሁን ማስተላለፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ። ከመረጃ አሞላል ጋር በተያያዘ የኢሜል አካውንት አከፋፈት የሚያሳይ አጋዥ ቪዲዮ በድረ ገፁ መጨረሻ ላይ የሚገኘውን [ Help ] የሚለውን ቁልፍ በመጫን መመልከት ይችላሉ። እናመሰግናለን!!